ኢትዮጵያ በታጁራ፣በርበራና ሞምባሳ ወደቦች ያላት የባህር ወደብ የአጠቃቀም ድርሻ እየጨመረ ነው

164


ግንቦት 18 ቀን 2014 (ኢዜአ)ቦት ኢትዮጵያ በታጁራ፣በርበራና ሞምባሳ ወደቦች ያላት የባህር ወደብ የአጠቃቀም ድርሻ ማደጉን የትራንስፖርና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ ገለጹ።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስድስተኛ ዙር አንደኛ ዓመት የሥራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው።

በጉባኤው የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ የ2014 ዓ.ም በጀት ዓመት የ10 ወር የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት አቅርበዋል።

በብሔራዊ የሎጅቲክስ ዘርፍ እቅድ አማካኝነት የባህር ወደብ አጠቃቀምን በማስፋት የሎጅስቲክስ ወጪና ጊዜን በመቆጠብ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ በትኩረት እየተሰራበት መሆኑን ሚኒስትሯ ገልጸዋል።

ለሎጅስቲክስ ሊወጣ የነበረውን ከሁለት ቢሊዮን ብር በላይ ገንዘብ ማዳን መቻሉን ተናግረዋል።

በበጀት ዓመቱ 10 ወራት የተለያዩ የባህር ወደብ አማራጮችን በመጠቀም ኢትዮጵያ በጅቡቲ ወደብ ያላትን የአጠቃቀም ድርሻ በ14 ነጥብ 62 በመቶ መቀነሷን አመልክተዋል።

ኢትዮጵያ ከጅቡቲ ወደብ በተጨማሪ የታጁራ፣በርበራና ሞምባሳ ወደቦችን እየተጠቀመች እንደምትገኝና የሶስቱ ወደቦች የኢትዮጵያን ጭነት የማስተናገድ ድርሻ እየጨመረ መምጣቱን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ የባህር ወደብ አጠቃም ድርሻ የጅቡቲ ወደብ 86 በመቶ፣የታጁራ ወደብ 9 ነጥብ 1 በመቶ፣የበርበራ ወደብ 5 በመቶ እና የሞምባሳ ወደብ 0 ነጥብ 02 በመቶ መሆኑን ነው ወይዘሮ ዳግማዊት ያስረዱት።

ለሎጅስቲክስ ሊወጣ የነበረውን 2 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ማዳን መቻሉን ተናግረዋል።
በበጀት ዓመቱ 10 ወራት አማካይ የመርከቦች የወደብ ላይ ቆይታን ከ15 ወደ 12 ቀናት ለመቀነስ ታቅዶ ወደ ዘጠኝ ማውረድ እንደተቻለም ጠቁመዋል።

15 ነጥብ 06 ሚሊዮን ቶን የገቢና ወጪ ንግድ ለማስተናገድ ታቅዶ 11 ነጥብ 09 ሚሊዮን ቶን ማስተናገድ መቻሉንም አክለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም