ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የፀጥታ አስከባሪ ሃይሎች ለከፈሉት መስዋእትነት እውቅና አሰጣጥ መርሃ ግብር ላይ ለመሳተፍ ዛሬ አሶሳ ገቡ

276


አሶሳ፣ ግንቦት 18 ቀን 2014 (ኢዜአ) የኢፌድሪ ጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የፀጥታ አስከባሪ ሃይሎች ለከፈሉት መስዋእትነት እውቅና አሰጣጥ መርሃ ግብር ላይ ለመሳተፍ ዛሬ አሶሳ ገብተዋል።


ከፊልድ ማርሻል ብርሃኑ በተጨማሪም ሌሎች የሀገር መከላከያ ከፍተኛ አመራሮችም ተገኝተዋል።


በዛሬው ዕለት በሃገር አቀፍ እንዲሁም በክልሉ የህግ ማስከበር ጥረት የፀጥታ አስከባሪ ሃይሎች ለከፈሉት መስዋእትነት እውቅና አሰጣጥ ፕሮግራም እንደሚካሄድ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የህዝብ ግንኙነት እና ፕሮቶኮል ዘርፍ ሃላፊ አቶ አድማሱ ተክሌ ለኢዜአ ተናግረዋል።


በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ለተገኘው አንፃራዊ ሰላም የሃገር መከላከያ እና የፌደራል ፖሊስን ጨምሮ የጋምቤላ፣ የደቡብ፣ የአማራ፣ የሲዳማ እና የክልሉ ልዩ ሃይሎች ሃላፊነታቸውን እየተወጡ መሆኑን አቶ አድማሱ አስታውሰዋል።


ከፍተኛ አመራሮቹን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ከልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሃሰን የክልሉ ምክር ቤት ምክትል ዋና አፈጉባኤ ወይዘሮ አለምነሽ ይባስ እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች በአሶሳ ህዳሴ አየር ማረፊያ ተገኝተው አቀባበል አድርገውላቸዋል።


ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️