ግብርናን ማዘመን የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባለፈ ሀገራዊ ብልፅግናን ለማስቀጠል ወሳኝ ነው

99


ግንቦት 17 ቀን 2014 (ኢዜአ) ግብርናን ማዘመን የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባለፈ ሀገራዊ ብልፅግናን ለማስቀጠል ወሳኝ መሆኑን የደቡብ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኡስማን ስሩር ተናገሩ።


የክልሉ ግብርና ቢሮ የ 9 ወር እቅድ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ በስልጤ ዞን ወራቤ ከተማ “የዘመነ ግብርና ለብልፅግና” በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ነው።


በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ክላስተር አስተባባሪና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኡስማን ስሩር በመድረኩ መክፈቻ ላይ እንደተናገሩት መድረኩ በግብርናዉ ዘርፍ የተሻሻሉ አሰራሮችና ተሞክሮዎች የልምድ ልውውጥ የሚደረግበት፣በዘርፉ በሚስተዋሉ ችግሮች ላይ ቀጣይ አቅጣጫ የሚቀመጥበት ነው ፡፡

ግብርናን ማዘመን የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባለፈ ሀገራዊ ብልፅግናን ለማስቀጠል ወሳኝ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡


መንግስት የግብርናን ስራ ከኋላ ቀር የአሰራር ስርዓት በማዉጣት የአርሶ አደሩንና የአርብቶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑንም የቢሮ ሃላፊው ገልጸዋል።


ግብርናን በማዘመን አመርቂ ዉጤት ለማምጣት የአመራሩን አቅም በማሳደግና የህብረተሰቡን ተሳትፎ በማጠናከር ዜጎችን ከድህነት ለማላቀቅና ሀገራዊ እድገቱን ለማረጋገጥ እየተሰራ ነው ብለዋል።


በመድረኩ የደቡብ ክልል ምክር ቤት የግብርና ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ግዛቸው ዋኖሬን ጨምሮ ከክልልና ከተለያዩ ዞኖች የተዉጣጡ አመራሮችና ባለድርሻ አካላት በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ፡፡


ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️