በኦሮሚያ ክልል ‘ቡሳ ጎኖፋ’ የተሰኘ ንቅናቄ ተጀመረ

103

ግንቦት 17 ቀን 2014 (ኢዜአ) በኦሮሚያ ክልል ‘ቡሳ ጎኖፋ’ የተሰኘ ንቅናቄ ተጀመረ ።

”ቡሳ ጎኖፋ” የገዳ ስርአት አካልና የኦሮሞ ሕዝብ ጥንታዊ የመረዳጃ ስርዓት ነው ተብሏል።

ስርዓቱ የኦሮሞ ህዝብ ሰው ሰራሽም ይሁን ተፈጥሯዊ ችግር ሲያጋጥመው ችግሩን ለማለፍ የሚታገዝበት ጥንታዊ ባህል ነው።

ንቅናቄውን ማስጀመር ያስፈለገበት ምክንያትም የህዝቡን የመረዳዳት ባህል ለማጎልበት ነው ተብሏል።

የክልሉ መንግስት ስርዓቱ ተቋማዊ መልክ እንዲኖረው ቢሮ ተደራጅቶ እየተመራ መሆኑም ታውቋል።

በንቅናቄው ማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ የተለያዩ የፌዴራልና የክልሉ የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ

‼️

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ

‼️

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ

‼️

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ

‼️