ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለአፍሪካ ቀን የመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክት አስተላለፉ

59

ግንቦት 17 ቀን 2014 (ኢዜአ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለአፍሪካ ቀን የመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክት በትዊተር ገጻቸው አስተላለፉ።

በመልዕክታቸው ለአህጉራዊ አንድነት ራዕይና ቀደምት አባቶች የሰነቁትን ሰላማዊ፣ የተሳሰረችና የበለጸገች አህጉር እውን ለማድረግ በቁርጠኝነት እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።

የአፍሪካ ቀን ግንቦት 17 (25 May) በአፍሪካውያን ዘንድ በየአመቱ የሚከበር ሲሆን ይህም አፍሪካውያን እ.አ.አ 1963 የአፍሪካ አንድነት ድርጅትን ያቋቋሙበትን ቀን ለማስታወስ ነው የሚከበረው፡፡

ቀኑ የሚከበረው እ.አ.አ ግንቦት 25 ቀን 1963 ነፃነታቸውን የተቀዳጁ 32 የአፍሪካ ሀገራት አዲስ አበባ ላይ ባደረጉት የመጀመሪያው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ጉባኤ ላይ ከተሰወነ በኋላ ነው።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ