አዲሱ የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼኽ ሞሐሙድ ስልጣን ተረከቡ

94

ግንቦት 16 ቀን 2014 (ኢዜአ) ተመራጩ የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼኽ ሞሐሙድ ከቀድሞው የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሞሃመድ አብዱላሂ (ፋርማጆ) ስልጣን ተረክበዋል፡፡

ከቀናት በፊት ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ያካሄደችው ሶማሊያ የህዝብ ተወካዮች አፈጉባኤና ምክትል አፈጉባኤ፣ ሚኒስትሮች፣ የመንግስት ሰራተኞች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት የፕሬዝዳንታዊ የስልጣን ርክክብ ስነ ስርዓት ተደርጓል፡፡

ዘጠነኛው የሃገሪቱ መሪ የነበሩት የቀድሞ የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሞሐመድ አብዱላሂ (ፋርማጆ) ለተመራጩ ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼኽ ሞሐሙድ ስልጣናቸውን አስረክበዋል፡፡

ተመራጩ የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼኽ ሞሐሙድ በሶማሊያ ፖለቲካ ትልቅ ድርሻ እንደነበራቸው የሚታወቅ ሲሆን ከፕሬዝደንት ሞሃመድ አብዱላሂ (ፎርማጆ) ቀደም ብለው ስምንተኛው ፕሬዝደንት በመሆን ሃገራቸውን አገልግለዋል።

ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼኽ ሞሐሙድ ከምርጫ በኋላ ባስተላለፉት መልእክት ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በሁለቱ አገሮች የጋራ ጉዳይ ላይ በትብብር እንደሚሰሩ መናገራቸው የሚታወስ ነው፡፡