በአሶሳ ከተማ ድብደባ በማካሄድ ግድያ የፈጸመው ግለሰብ በ20 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጣ

98

ግንቦት 15 ቀን 2014 (ኢዜአ) የአሶሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በከባድ የሰው ግድያ ወንጀል የተከሰሰውን ግለሰብ በ20 ዓመት ጽኑ እስራት ቀጣ፡፡

የፍርድ ቤቱ ፕሬዝዳንት አቶ አምነላ ሰበባ ለኢዜአ እንዳሉት ተከሳሽ መላኩ ይዘንጋው የተባለ ግለሰብ በከተማው ወረዳ ሁለት ጥር 17 / 2014 ዓ.ም. አንድ ግለሰብ በጭካኔ በዱላ ጭንቅላቱን በመደብደብ ህይወቱ እንዲያልፍ አድርጓል፡፡

እንዲሁም የተከሳሹን አስክሬን በስልክ ሽቦ ጠምጥሞ ማዳበሪያ ውስጥ በመክተት ከፍሳሽ መውረጃ ውስጥ መጨመሩን ፕሬዝዳንቱ ገልጸዋል፡፡

ተከሳሹ የፈጸመው ከባድ የሰው ግድያ ወንጀል በአቃቢ ህግ የሰው የህክምና እና የሰነድ ማስረጃ መረጋገጡን ጠቁመዋል፡፡

ተከሳሹ የቀረበበትን ወንጀል ሊከላከል ባለመቻሉ ፍርድ ቤቱ ዛሬ በአሶሳ ከተማ በዋለው ችሎት ተከሳሹ በ20 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ መወሰኑን አስረድተዋል፡፡

ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ

‼️

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ

‼️

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ

‼️

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ

‼️
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም