ዩኒቨርስቲው አዲስ ገቢ ተማሪዎችን እየተቀበለ ይገኛል

84

ሆሳዕና:ግንቦት 15/2014 (ኢዜአ) የወራቤ ዩኒቨርስቲ ከ3 ሺህ 200 በላይ አዲስ ገቢ ተማሪዎችን ዛሬ እየተቀበለ ነው ።

የወራቤ ዩኒቨርሲቲ ለአዲስ ገቢ ተማሪዎች ከመናኸሪያ ጀምሮ የትራንስፖርት አማራጭ በማቅረብ ጭምር አቀባበል እንዳደረገላቸው ተገልጿል።

በዩኒቨርሲቲው ነባር ተማሪዎችና ከወራቤ ከተማ የተውጣጡ ወጣቶች በመቀናጀት ነው ለተማሪዎቹ አቀባበል እያደረጉ የሚገኙት ።

በቅበላ መርሐ ግብሩ ላይ የዩኒቨርሲቲውና የዞኑ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችን ጨምሮ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር  ሽማግሌዎችና የአካባቢው ነዋሪ ማህበረሰብ ተገኝተዋል።