ዳያስፖራው በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸው የትምህርት ተቋማት መልሶ ግንባታ ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ ቀረበ

68

ግንቦት 15 ቀን 2014 (ኢዜአ) አሸባሪው የህወሓት ቡድን ጉዳት ያደረሰባቸውን የትምህርት ተቋማት መልሶ ለመገንባት ዳያስፖራው እገዛ እንዲያደርግ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ጥሪ አቀረቡ፡፡

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ጥሪውን ያቀረቡት በኢንግሊዝ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በለንደን ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራንና ተመራማሪዎች ጋር ባካሄዱት ውይይት ላይ ነው፡፡

በውይይቱ ወቅት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ባደረጉት ንግግር፥ በሁሉም የትምህርት እርከን እየተካሄደ ያለው ማሻሻያ ለመጪው የኢትዮጵያ ትውልድ የተሻለች ሀገር ለማስረከብ መሰረት የሚጥል ነው ብለዋል፡፡

May be an image of 8 people, people sitting and people standing

በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ዳያስፖራ ባለሙያዎች ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።

አክለውም የዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በተከሰቱ ግጭቶች የተጎዱ ትምህርት ቤቶችን መልሶ ለመገንባት ለሚደረገው ሀገራዊ ጥረት የበኩላቸውን እንዲወጡም ጥሪ ማቅረባቸውን በእንግሊዝ ከኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡