በሀዋሳ “ ለአረጋዊያን ክብር እንጓዛለን ” በሚል መሪ ሀሳብ የእግር ጉዞ እየተካሄደ ነው

83

ሀዋሳ ፤ ግንቦት 14 ቀን 2014 (ኢዜአ) በሀዋሳ “ለአረጋዊያን ክብር እንጓዛለን” በሚል መሪ ሀሳብ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የተሳተፉበት የእግር ጉዞ በመካሄድ ላይ ነው ።

በመርሀ-ግብሩ ላይ የሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ መስራችና ዋና ስራ አስኬያጅ ሲስተር ዘቢደር ዘውዴ፣ታዋቂ አርቲስቶች፣ የመገናኛ ብዙሀን ባለሙያዎች፣ የመንግስት የሥራ ኃፊዎች፣ እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል ።

May be an image of 8 people, people standing and outdoors

የእግር ጉዞው ዋና ዓላማው ትናንት ታሪክ የሰሩ አሁን ግን በብዙ ችግር ውስጥ የሚገኙ አቅመ ደካማ አረጋዊያንን በተቻለ ሁሉ የመደገፍ ባህልን ማዳበርና ተሳትፎ መጨመር ነው ተብሏል።

በሁሉም እድሜ ክልል ያሉ የህብረተሰብ ክፍሎች በዚህ የእግር ጉዞ እየተሳተፉ ይገኛሉ።