“የመከላከያ ዋር ኮሌጅ ምሩቃን ዕውቀትን ሳያቋርጡ መፈለግና ለሌሎችም ማጋራት አለባቸው”-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ

92

ግንቦት 13 ቀን 2014 (ኢዜአ) የመከላከያ ዋር ኮሌጅ ምሩቃን ዕውቀትን ሳያቋርጡ መፈለግና ለሌሎችም ማጋራትን እንዲቀጥሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አሳሰቡ።

ኮሌጁ በልዩ ልዩ ዘርፍ የተሰማሩ ሙያተኞችን አሰልጥኖ አስመርቋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኢፌዲሪ መከላከያ ዋር ኮሌጅ የመጀመሪያ ዙር የምረቃ ሥነ ሥርዓት ላይ ተገኝተው መልዕክት አስተላልፈዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በስነ ሰርዓቱ ወቅት ምሩቃኑ ዕውቀትን ሳያቋርጡ መፈለግና ለሌሎችም ማጋራትን እንዲቀጥሉ አሳስበዋል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ

‼️

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ

‼️

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ

‼️

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ

‼️