ተመድ በኢትዮጵያ የጾታዊ እኩልነትን ለማረጋገጥ በሚያግዝበት ጉዳዮች ዙርያ ምክክር ተካሄደ

246

ግንቦት 12 ቀን 2014 (ኢዜአ)የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሴቶች ጉዳይ በኢትዮጵያ ተወካይ አና ሙታቪቲ ጋር የጾታዊ እኩልነትን ለማረጋገጥ በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙርያ ተወያይተዋል።

ውይይቱ ተመድ በኢትዮጵያ የስርዓተ ጾታ እኩልነትን ለማረጋገጥ በአራት አመታት ውስጥ ከሚኒስቴሩ ጋር በሚያከናውናቸው ተግባራት ላይ ያተኮረ መሆኑ ተመልክቷል።

በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል ጉዳት የደረሰባቸውን ሴቶች ከመደገፍ አንጻርም በጋራ ስለሚከናወኑ ጉዳዮች በውይይቱ መነሳቱ ተነግሯል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም