ኢትዮ-ቴሌኮም የሞጁላር መረጃ ማዕከልን በጋራ ለመጠቀም የሚያስችል ሥምምነት ከተለያዩ የፋይናንስ ተቋማት ጋር ተፈራራመ

142

ግንቦት 12 ቀን 2014 (ኢዜአ) ኢትዮ-ቴሌኮም የሞጁላር መረጃ ማዕከልን በጋራ ለመጠቀም የሚያስችል ሥምምነት ከተለያዩ የፋይናንስ ተቋማት ጋር ተፈራረመ።

ተቋሙ ሥምምነቱን የተፈራረመው ከዘመን፣ ከዘምዘምና ሂጅራ ባንክ እንዲሁም ሬስ ማይክሮ ፋይናንስና ከዌብስክሪብስ የፋይናንስ ተቋማት ጋር ነው።

የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ እንደተናገሩት፤ በኢትዮጵያ ዲጂታል ኢኮኖሚ ለመገንባት እንደ ዳታ ማዕከል ዓይነት አሰራር መዘርጋት ወሳኝ ነው።

የመረጃ ማዕከሉን በጋራ ለመጠቀም ሥምምነት የገቡ ተቋማት  የአገልግሎት አሰጣጥ  አቅም ከማሳደግ  ባለፈ ጥራትን የሚጨምር  መሆኑን  አብራርተዋል።

በአሁኑ  ወቅት በፋይናንስ ዘርፍ  የአገልግሎት  ተጠቃሚ  ቁጥር እየጨመረ መሆኑን  ጠቁመው   ፍላጎቱን በዘመናዊ  ቴክኖሎጂ መመለስ  ይገባል ብለዋል።

ኢትዮ-ቴሌኮም ባለፉት ጥቂት ዓመታት አዳዲስ  አሰራር  እየዘረጋ መሆኑን  ጠቅሰው ወደ ፊትም አጠናክሮ እንደሚቀጥል አብራርተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም