የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡለትን ከ4 ሺህ በላይ አዲስ ገቢ ተማሪዎች እየተቀበለ ነው

175

ሆሳዕናግንቦት11/2014(ኢዜአ)የዋቸሞዩኒቨርሲቲ ዘንድሮ የተመደቡለትን ከ4 ሺህ 600 በላይ ተማሪዎችን ከትናንት በስትያ ጀምሮ  መቀበል መጀመሩን ገልጿል።

ከተለያየ የሃገሪቱ ክፍል ወደ የኒቨርሲቲው የተመደቡ አዲስ ገቢ ተማሪዎች  ከቡድናዊና ከብሔርተኝነት አስተሳሰብ በመራቅ ለሰላማዊ የመማር ማስተማር ስኬታማነት እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሕዝብን  አብሮነት  እሴት  ለመሸርሸር   እየተደረገ   ያለውን ሴራ  በማክሸፍ  የሚጠበቅባቸውን እንደሚወጡና ተማሪዎች  የነገ ሀገር ተረካቢ በመሆናቸው ለሠላም መስፈን በአርአያነት ሊንቀሳቀሱ እንደሚገባም እንዲሁ፡፡

በተመደቡበት የትምህርት መስክ ጠንክረውበመማር የሀገርና የቤተሰብ ኩራት በመሆን የጥፋት ኃይሎች በሚዘረጉት ወጥመድ ተሰናክሎ ላለመቅረት ማስተዋል እንደሚገባም ነው የገለፀት ፡፡

የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሀብታሙ አበበ ዩኒቨርሲቲው እንደ ሀገር የተሰጠውን ተልዕኮ ለመወጣት እየተንቀሳቀሰ መሆኑን አስታውቀዋል።

በትምህርት ሚኒስቴር የተመደቡለትን  ከ4 ሺህ 600  በላይ ተማሪዎችን   ከትናንት በስትያ ጀምሮ እየተቀበለ መሆኑንም ገልጸዋል።

ዩኒቨርሲቲው ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በመቀናጀት የአካባቢውንና የተማሪዎቹን ሰላምና አብሮነት ለማጠናከር ባደረገው እንቅስቃሴ ለአቻ ተቋማት ተምሳሌት ለመሆን ጥረቱን እንደማያቋርጥም አረጋግጠዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም