በኢትዮጵያ የተጀመረው በምግብና በመሠረታዊ ሸቀጦች ራስን የመቻል ጉዞ በዘላቂነት እንዲሳካ ምርታማነት ባህል ሊሆን ይገባል– ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ

84

ግንቦት 10 ቀን 2014 (ኢዜአ) በኢትዮጵያ የተጀመረው በምግብና በመሠረታዊ ሸቀጦች ራስን የመቻል ጉዞ በዘላቂነት እንዲሳካ ምርታማነት ባህል ሊሆን ይገባል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት በሀገራችን ምርታማነትን ለመጨመር የሚያስችሉ ሰፊ እድሎች አሉ ብለዋል።

በዚህም “በኢትዮጵያ የተጀመረው በምግብና በመሠረታዊ ሸቀጦች ራስን የመቻል ጉዞ በዘላቂነት እንዲሳካ ምርታማነት ባህል ሊሆን ይገባል” ነው ያሉት።

እምቅ የተፈጥሮ ሐብት፣ ምቹ አየር ንብረት፣ ለም መሬት፣ ሰፊ የውሃ ሃብት፣ የሰው ኃይል አለን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ እነዚህን በበቂ ጥቅም ላይ ያልዋሉ ሐብቶችን በማገናኘት ምርታማነትን መጨመር አለብን በማለት አመልክተዋል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ 

‼️

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ

‼️

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ

‼️

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ

‼️