ኢትዮጵያንና ሌሎች ሀገራትን በፀሓይ ኃይል ዘርፍ ተጠቃሚ የሚያደርግ የአንድ ትሪሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት ፍኖተ ካርታ ሊቀርብ ነው

152

ግንቦት 8 ቀን 2014 (ኢዜአ) ኢትዮጵያንና ሌሎች የዓለም ፀሓይ ሃይል ሕብረት አባል ሀገራትን በዘርፉ ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያስችል የአንድ ትሪሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት ፍኖተ ካርታ ሊቀርብ መሆኑ ተገለጸ።

የዓለም ፀሓይ ሃይል ሕብረት “ቀጣይነት ያለው የኃይል አቅርቦት ለሁሉም” በሚል መሪ ሃሳብ ከፀሓይ የሚገኘውን የኃይል ተጠቃሚነት የሚያሳድግ ፎረም በሩዋንዳ ኪጋሊ ከግንቦት 9 እስከ 11 2014 ዓ.ም ድረስ እንደሚካሄድ ገልጿል።

በዚህ ፎረም ዘርፉን በከፍተኛ ደረጃ የሚያሳድጉ የኢንቨስትመንት አጀንዳዎች እንደሚነሱበት የገለጸው ሕብረቱ፤ይህንኑ የሚያጠናክር ስምምነት በሕብረቱና በአለም የተፈጥሮ ሀብት ኢንስቲትዩት መካከል መካሄዱን አመልክቷል።

በስምምነቱ መሠረት ሁለቱ ተቋማት ኢትዮጵያን ጨምሮ የዓለም ፀሓይ ሃይል ሕብረት አባል ሀገራትን ተጠቃሚ የሚያደርግ አንድ ትሪሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት የሚስብ ፍኖተ ካርታ በፎረሙ ላይ እንደሚያቀርቡ አስታውቋል።

የዓለም ፀሓይ ሃይል ሕብረትን 86 ሀገራት ፈርመው ያጸደቁ ሲሆን የአባል ሀገራቱ ህዝቦችን በፀሓይ ሃይል ተጠቃሚ የሚያደርጉ ተግባራትና እንቅስቃሴዎች እንደሚያከናውኑበት ተመልክቷል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ

‼️

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ

‼️

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ

‼️

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ

‼️