የሀገራት መሪዎች በአፍሪካ የሚመረቱ የኮቪድ-19 ክትባቶችን ተደራሽነት በተመለከተ ምክክር አካሄዱ

114

ግንቦት 8 ቀን 2014(ኢዜአ)ፕሬዚዳንት ሣኅለ ወርቅ ዘውዴን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራት መሪዎች በአፍሪካ የሚመረቱ የኮቪድ-19 ክትባቶች ተደራሽነትን በተመለከተ ምክክር ማካሄዳቸው ተገለጸ።

የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ በአፍሪካ የሚመረቱ የኮቪድ-19 ክትባቶችን በተመለከተ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ባዘጋጀው የበይነ መረብ ስብሰባ ላይ መሳተፋቸውን የፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት ገልጿል።

ምክክሩ የአፍሪካ የኮቪድ-19 የክትባት ምርት የዓለም አቀፍ የገበያና የሥርጭት መድረኮች ውስጥ መግባት ስለሚችልበት መንገድ ላይ ያተኮረ ነበር ተብሏል።

በመድረኩ የሩሲያና የዩክሬን ጦርነት በአፍሪካ የምግብ ዋስትና ላይ እያመጣ ስላለው ቀውስ አህጉራዊ መፍትሄ ማበጀት እንደሚያስፈል የሀገር መሪዎች አበክረው መናገራቸው ነው የተነገረው።

በስብሰባው ላይ የተጋበዙት አገራት ክትባት ለማምረት አቅም ያላቸውና አቅም እየገነቡ ያሉ አገሮች መሪዎች ናቸው የተባለ ሲሆን የፈረንሳይ ፕሬዚደንትና የአውሮፓ ሕብረት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት በእንግድነት መሳተፋቸው ተመልክቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም