ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀመድ የእንኳን ደስ ያልዎት መልዕክት አስተላለፉ

92

ግንቦት 8 ቀን 2014 (ኢዜአ)ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀሙድ በድጋሚ የሶማሊያ ፌደራላዊ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ሆነው ''በመመረጥዎ እንኳን ደስ ያለዎት ለማለት እወዳለሁ''ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ''የጋራ በሆኑ የሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ተቀራርበን እንደምንሠራ እምነቴ ነው''ያሉት ።

የሶማሊያ ፓርላማ በመጨረሻው ዙር ምርጫ የቀድሞውን ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀመድን 10ኛው የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት አድርጎ መርጧል።

ትናንት በተካሄደው ምርጫ የመጨረሻ ድምፅ አሰጣጥ ሃሰን ሞሀመድ ስልጣን ላይ የነበሩትን መሀመድ አብዱላሂ ፋርማጆን በማሸነፍ ነው የተመረጡት።

በሶማሊያ ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ በሰፊ የድምፅ ልዩነት ያሸነፉት ሀሰን ሼክ መሃመድ ምርጫው በተጠናቀቀ ጥቂት ሰአታት ውስጥ 10ኛው የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሆነው ቃለ መኃላ ፈፅመዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም