በደንዲ ሀይቅ ላይ ዘመናዊ የኢኮ-ቱሪዝም ሎጂ ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ

144

ግንቦት 07 ቀን 2014 (ኢዜአ) የገበታ ለሀገር ፕሮጀክት አካል በሆነው የደንዲ ሃይቅ ላይ ዘመናዊ ኢኮ-ቱሪዝም ሎጂ ለመገንባትየመሰረት ድንጋይ ዛሬ ተቀመጠ።

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ከአዲስ አበባ 127 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል የደንዲ ሐይቅ።

የመሰረት ድንጋዩን የኦሮሚያ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ የጣልያኑ “ዊ ቢውልድ” ኮንስትራክሽን ድርጅት ዋና ስራ አስፈፃሚ ፒዬትሮ ሳሊኒ እና የመከላከያ ሚኒስትር ዶክተር አብርሃም በላይ አስቀምጠዋል።

በመርሀ ግብሩ ላይ ከፍትኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችና የአካባቢው ነዋሪዎች መገኘታቸውን የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ መረጃ ያመለክታል።

የገበታ ለሃገር ፕሮጀክት ዋና ዓላማ በቅድሚያ የአካባቢውን ማህበረሰብ ተጠቀሚነት ማረጋግጥ ስለመሆኑ በዚሁ እለት ተጠቁሟል።

በገበታ ለሀገር የሚለማው የወንጪ – ደንዲ የተቀናጀ ኢኮ ቱሪዝም ፕሮጀክት መጋቢት 11 ቀን 2013 ዓ.ም የግንባታ ስራው በጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ መጀመሩ ይታወሳል።