ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ፕሬዚዳንት ህልፈት የተሰማቸውን ሐዘን ገለጹ

196

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 05 ቀን 2014 (ኢዜአ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ፕሬዚዳንት ሼክ ካሊፋ ቢን ዛይድ አል-ናህያን ህልፈት የተሰማቸውን ሐዘን ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ ለተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች አልጋ ወራሽ ሼክ ሞሃመድ ቢንዛይድ አል-ናህያን እንዲሁም ለተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ህዝብ የተሰማኝን ጥልቅ ሐዘን እገልጻለሁ ብለዋል።

የ73 ዓመቱ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ፕሬዚዳንት ሼክ ካሊፋ ቢን ዛይድ አል-ናህያን ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ዛሬ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

እ.አ.አ ከ2004 ጀምሮ አገሪቱን በፕሬዚዳንትነት ያገለገሉት ሼክ ካሊፋ ቢን ዛይድ አል-ናህያን ህልፈታቸውን ተከትሎ የ40 ቀን ሃዘን እንደሚታወጅ የፕሬዚዳንታዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም