የሩሲያ የድል በዓል ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሰዎች በተሳተፉበት ልዩ ዝግጅትና ወታደራዊ ትርኢት ተከበረ

221

ግንቦት 02 ቀን 2014 (ኢዜአ) ሩሲያ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት በናዚ ጀርመን ላይ የተጎናጸፈችውን ድል ተከትሎ የሚከበረው የሩሲያ የድል በዓል ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሰዎች በተሳተፉበት ልዩ ዝግጅትና በወታደራዊ ትርኢት መከበሩ ተገለጸ።

ስፑትኒክ የሩሲያን የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴርን ጠቅሶ እንደዘገበው፤ 77ኛው የቀድሞ ሶቭየት ሕብረት የድል በዓል በሩሲያና በቤላሩስ ከተሞች በልዩ ልዩ ወታደራዊ ትርኢቶች ተከብሯል።

በክብረ በዓሉ ከ15ሺ በላይ ፌስቲቫሎች መከናወናቸውን የገለጸው ሚኒስቴሩ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሰዎች በበዓሉ ላይ መሳተፋቸውን አስታውቋል።

ፕሬዚዳንት ፑቲንም በክበረ በዓሉ ላይ ከናዚ ጀርመን ጋር በነበረው ውግያ ያለፉትን የአባታቸውን ፎቶ ይዘው የታዩ ሲሆን በዓሉን አስመልክቶ ወቅታዊ ሁኔታን የዳሰሰ ንግግር አድርገዋል።

በ77ኛው የድል በዓል ሞስኮ ድሉን በሚያበስሩ መግለጫዎች፣ ባንዲራዎችና ልዩልዩ ስነ ስርዓቶች ደምቃ እንደነበር መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ