ኢትዮ ቴሌኮም የ5G የሞባይል ኔትወርክ አገልግሎት ጅማሮን አበሰረ - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮ ቴሌኮም የ5G የሞባይል ኔትወርክ አገልግሎት ጅማሮን አበሰረ

ግንቦት 01 ቀን 2014 (ኢዜአ) ኢትዮ ቴሌኮም የ5ኛ ትውልድ(5G) የሞባይል ኔትወርክ አገልግሎት መጀመሩን አስታወቀ።
ዓለም የደረሰችበት የመጨረሻው ፈጣኑ ኔትወርክ የቻይናው ህዋዌ የፈጠረው አምስተኛ ትውልድ(5G) የተሰኘው የኔትወርክ አገልግሎት ነው።
የ5G ቴክኖሎጂ የግለሰቦችን ዕለታዊ እንቅስቃሴ የማሻሻልና የኢንዱስትሪዎችን የስራ ክንውን ለማቀላጠፍ ሚናው ከፍተኛ እንደሆነ ታውቋል፡፡
5ኛው ትውልድ ኢንተርኔት ከ4ኛው ትውልድ ቴክኖሎጂ ሲነፃፀር ከ100 እጥፍ ጊዜ በላይ ፍጥነት ሲኖረው በሰከንድ እስከ 100 ጊጋ ባይት መረጃ የመለዋወጥ እንደሚያስችልም መረጃዎች ያሳያሉ፡፡
ኢትዮ-ቴሌኮም ቀደም ብሎ በአዲስ አበባ ብቻ ተወስኖ የቆየውን የ4ጂ ሞባይል ኔትዎርክ አገልግሎት በመላው አገሪቱ በማስፋፋት ከ136 በላይ ከተሞችን ተጠቃሚ አድርጓል።
ኩባንያው የዘረጋቸው የ4ጂ ሞባይል ኔትዎርክ ማስፋፊያ መሰረተ ልማቶች ለ5G ሞባይል ኔትዎርክ ዝግጁ ተደርገው የተሰሩ መሆናቸውን መግለፁ ይታወሳል።
ከ65 ሚሊዮን በላይ የሞባይል ደንበኞች ያሉት ኢትዮ ቴሌኮም 25 ሚሊዮን ደንበኞቹ የሞባይል ኢንተርኔት ተጠቃሚዎች እንዳለውም መረጃዎች ያሳያሉ፡፡
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ በዛሬው ዕለት ኩባንያው ላለፉት ወራት ያደረገውን ሙከራ አጠናቆ የአምስተኛ ትውልድ ሞባይል ኔትዎርክን መጀመሩን ይፋ አድርገዋል፡፡
አገልግሎቱ ማብሰሪያ መድረኩ በሚደረግበት በሸራተን አካባቢ በአሁኑ ሰዓት በይፋ ጀምሯል።
ኢትዮ ቴሌኮሞ ዲጂታል ኢትዮጵያን ዕውን ለማድረግ እየሰራ ነው ብለዋል። ፍጥነት ብቻ ሳይሆን ከሌሎች ኔቶወርኮቾ በተለዬ ብዙ መልካም ጎኖች አሉት ብለዋል።
2121