በሐረሪ ክልል ከ800 ዓመታት በላይ ያስቆጠሩ መጻህፍትን የያዘ "ማኑስክሪፕት" ሙዚዬም ተመረቀ

163

ሚያዝያ 30 ቀን 2014 ኢዜአ) በሐረሪ ክልል ከ800 ዓመታት በላይ ያስቆጠሩ መጻህፍትን የያዘ "ማኑስክሪፕት" ሙዚዬም ተመረቀ።

ሙዚዬሙን የባህልና ስፖርት ሚኒስትር አቶ ቀጄላ መርዳሳና "ከኢድ እስከ ኢድ ወደ አገር ቤት ጉዞ" ጣምራ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዑስታዝ አቡበከር አህመድ መርቀውታል።


ሙዚዬሙ በውስጡ የታሪክና እስላማዊ መጻህፍት እንደያዘና መጻህፍቱ በከርቤና ጥላሸት ይፃፉ እንደነበር በምረቃው ሥነ ሥርዓት ላይ ተገልጿል።

የሐረሪ ክልል ባህል ቅርስና ቱሪዝም ቢሮ የማኑስክሪፕት ሙዚዬም አማካሪ ዕጩ ዶክተር አብዱልሀሚድ አብዱላሂ "ሙዚዬሙ ሐረር ውስጥ ያሉ በእጅ የተፃፉ ጥንታዊ መጻህፍት ያሉበትን ሁኔታ ያሳያል" ብለዋል።

ሙዚየሙ የሐረርን ታሪክ የሚያሳዩ የእስልምና መናገሻዎችን መሰረት ያደረጉ የታሪክ፣ የመልክዓ ምድር(ጂኦግራፊ)፣ የሳይንስ፣ የቋንቋ መጸህፍት መያዙን አስታውቀዋል።

ሙዚየሙ ሀገር በቀል እውቀትን ሳይጠፋ ለተተኪው ተውልድ ለማስተላለፍ ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለውም እጩ ዶክተር አብዱልሀሚድ ተናግረዋል።

ጥንታዊ መጻህፍት በከርቤና ጥላሸት ይፃፉ እንደነበር ዕጩ ዶክተር አብዱልሀሚድ ገልጸዋል።

በምረቃው ሥነ ሥርዓት ላይ የሐረሪ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ሱልጣን አብዱሰላምን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ አመራሮችና እንግዶች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም