ኢቢሲ በሐረሪ ክልል ያስገነባቸውን የቴሌቪዥንና የሬዲዮ ስቱዲዮዎችን አስመረቀ

123

ሚያዚያ 30 ቀን 2014 (ኢዜአ)የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፕሬሽን (ኢቢሲ) በምስራቁ የአገሪቱ ክፍል ተደራሽነቱን ለማስፋት በሐረር ከተማ ያስገነባቸውን የቴሌቪዥንና የሬዲዮ ስቱዲዮዎችን አስመረቀ።

በምረቃው ስነ ስርዓት የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ፣የአቢሲ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ፍስሃ ይታገሱና ሌሎች የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

በስቱዲዎቹም መከፈት የአካባቢውን ታሪክ፣ባህልና ትውፊት የተመለከቱ ጉዳዮች ላይ ዜና እና ፕሮግራሞችን ለታዳሚ ለማድረስ እንደሚያስችል ተገልጿል።

May be an image of 2 people and indoor

የኢትዮዽያ ሬድዮ ለምስራቁ አገሪቱ ክፍል ህዝብ ተደራሽነት ማዕከሉን ሐረር ከተማ ያደረገ ስርጭት በጥቅምት ወር 1965 ዓም የጀመረ ሲሆን በ2004 ዓም ተቋርጦ ቆይቷል።

በአካባቢው ማህበረሰብ ቋንቋ የሬድዮ ስርጭት መጀመሩም ለአካባቢው ማህበረሰብ ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለውም ይታወቃል።