ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን “ከኢድ እስከ ኢድ ወደ ሀገር ቤት ጥሪ” ከመጡ የዳያስፖራ አባላት ጋር ተወያዩ

157

ሚያዝያ 29 ቀን 2014 (ኢዜአ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በ “ከኢድ እስከ ኢድ ወደ ሀገር ቤት” ጥሪ ከመጡ ዳያስፖራ አባላት ጋር መወያየታቸው ተገለጸ።

አቶ ደመቀ የተወያዩት በ “ከኢድ እስከ ኢድ ወደ ሀገር ቤት” ጥሪ ከእንግሊዝ ሀገር ከመጡ የዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላት ጋር ሲሆን በተለያዩ ጉዳዮች ዙርያ መምከራቸው ተገልጿል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፤ ቀደም ሲል ኢድን በአገር ቤት እናክብር በማለት “ታላቁ የኢድ ሰላት በኢትዮጵያ” በሚል መሪ ቃል ለኢትዮጵያዊያንና ትውልደ-ኢትዮጵያዊያን እንዲሁም ለኢትዮጵያ ወዳጆች ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል።