ዐርበኝነት ማለት በሀገር ጉዳይ ላይ ለእውነትና ለእምነት የሚከፈል መሥዋዕትነት ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ

113

ሚያዚያ 27 ቀን 2014 (ኢዜአ) ጀግኖች እናቶቻችን እና አባቶቻችን የሀገራቸውን ነጻነትና ሉዓላዊነት ለመጠበቅ ሲሉ ምትክ የሌለውን ሕይወታቸውን ከፍለዋል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ እየተከበረ ያለውን 81ኛውን የድል ቀን አስመልክቶ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው መልዕክት አስተላልፈዋል።

ዛሬ ይሄንን የሕይወት ዋጋ የከፈሉትን ዐርበኞቻችንን በክብር እናስባቸዋለን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ እኛም ልጆቻቸው፣ ቀደምት ዐርበኞች ላከበሯት ሀገራችን ልዕልናና ብልጽግና ለማጎናጸፍ ዋጋ የምንከፍል ተተኪ ዐርበኞች መሆናችንን ልናረጋግጥ ይገባናል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም