የሲዳማ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ የክልሉን ተጨማሪ በጀትና ሹመትን በማፅደቅ ተጠናቀቀ

162

ሀዋሳ፤ ሚያዝያ 26 ቀን 2014 (ኢዜአ) የሲዳማ ክልል ምክር ቤት ስድስተኛ ዙር አንደኛ የሥራ ዘመን ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ የክልሉን ተጨማሪ በጀትና የዳኞችን ሹመት በማፅደቅ ተጠናቅቋል።

ምክር ቤቱ የክልሉን ተጨማሪ የ874 ሚሊዮን ብር በጀት በሙሉ ድምፅ ያፀደቀ ሲሆን በጀቱም የውስጥ ገቢን በማሻሻል የሚመነጭ መሆኑ ተመላክቷል።

ከዚህ በተጨማሪም ምክር ቤቱ ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የአራት ዳኞችንና በየደረጀጃው ለሚገኙ ፍርድ ቤቶች የ15 ዳኞችን ሹመት በሙሉ ድምፅ በማጽደቅ ጉባኤውን አጠናቋል።

የተሾሙት ዳኞች በምክር ቤቱ አባላት ፊት ቀርበው ቃለ መሀላ መፈጸማቸውን ሪፖርተራችን ከስፍራው ዘግቧል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም