በደቡብ ክልል 1ሺህ 443ኛው የኢድ አል ፈጥር በዓል ያለምንም የጸጥታ ችግር ተከብሯል-ፖሊስ ኮሚሽን

102

ሀዋሳ ሚያዚያ 24/2014 (ኢዜአ) በደቡብ ክልል 1443ኛው የኢድ አል ፈጥር በዓል ያለምንም የፀጥታ ችግር በሰላም ተከብሮ መጠናቀቁን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ህዝብ ግንኙነት ዲቪዥን ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ታጁ ነጋሽ  እንዳስታወቁት በአሉ ያለምንም የጸጥታ ችግር ተከብሮ ተጠናቋል ።

ህዝበ ሙስልሙ በዓሉን በሰላም እንዲያከብር ለማስቻል የጸጥታ ሃይሉ የተቀናጀ የጸጥታ ማስከበር ስራ ማከናወኑን ተናግረዋል።

በተለይ በድንገት ሊከሰቱ የሚችሉ የፀጥታ ችግሮችን አስቀድሞ ለመከላከል እንዲቻል አሳታፊ  የሆነ የፀጥታ እቅድ በማዘጋጀት በተቀናጀና በተደራጀ መልኩ መተግበሩን አመልክተዋል ።

በክልሉ በሁሉም አከባቢዎች ተገቢው ቅድመ ዝግጅት ተደርጎ እንደነበር ገልጸው የወንጀልም ሆነ ድንገተኛ የተሽከርካሪ አደጋ ሳይመዘገብ በዓሉ በሰላም መጠናቀቁን አስታውቀዋል።

"መላዉ የክልሉ ህዝብ በዓሉ ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ከፓሊስና ከሌሎች የፀጥታ ኃይሎች ጋር በመሆን ላበረከተው አስተዋጾ ኮሚሽኑ ታላቅ አክብሮትና ምስጋና አለው" ብለዋል ።

የክልሉ የህዝብ  የሁሉ መሰረት የሆነው ሰላም በፀረ-ሰላም ግለሰቦችም ሆነ ቡድኖች እንዳይደፈርስ ለፀጥታ ኃይሎች የሚያደርገውን ድጋፍና ትብብር አጠናክሮ እንዲቀጥል ዋና ኢንስፔክተር ታጁ ጥሪ አቅርበዋል ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም