የኢድ አልፈጥር በዓል በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች በድምቀት እየተከበረ ነው

105

ክልል፤ ሚያዚያ 24/ 2014(ኢዜአ) 1ሺህ 443ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል በተለያዩ የሀገሪቱ አከባቢዎች በድምቀት እየተከበረ ነው።

በዓሉ እየተከበረባቸው ካሉት አካባቢዎች መካከል  ሀዋሳ፤ ባህርዳር ፣አዳማ ድሬደዋ፣   ሐረር፣ ሰመራ ፣  ጋምቤላ፣ ደሴ፣ ገንዳ ውሃ፣ ደብረ ማርቆስ፣ ደብረ ብርሃን፣ ጅማ ፣ ጉባ፣ መቱ፣ ዲላ፣ሆስዕና አርባምንጭና  ጂንካ ከተሞች  ይገኙበታል።  

በሀዋሳ  ከከተማዋ የተለያዩ   አቅጣጫዎች ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ ህዝበ ሙስሉሙ ወደ አደባባይ በመትመም ሃይማኖታዊ ስርዓቱ በሚያዘው መሰረት በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።

በሀዋሳ ሚሊኒየም አደባባይ እየተከበረ ባለው ኢድ አልፈጥር በዓል የከተማዋ የእስልምና እምነት ተከታዮች የኢድ ሶላት ስግደት ስነ-ስርዓት እያካሄዱ ነው።

በድሬዳዋ ከተማ 1ሺህ 443ኛው  በብዙ ሺ የሚቆጠሩ የሙስሊሙ ማህበረሰብ  በድምቀት እያከበረ ነው።

በበዓሉ አከባበር ስነ-ስርዓት  የእስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት አመራሮች ፤ዑላማዎች፤ሼኾች ፤ዑጋዞችና ሌሎችም የእምነቱ ተከታዮች እየተሳተፉ ነው።

የኢድ አልፈጥር በዓል በባህር ዳር ብሄራዊ ስታዲየም ሃይማኖታዊ ስርዓቱን ጠብቆ ከጥዋቱ 12  ሰዓት ጀምሮ  በድምቀት እየተከበረ  የሚገኝ ሲሆን  በአማራ  ክልል  ሌሎችም  ከተሞችም እንዲሁ።

በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ  በርካታ የእምነቱ ተከታዮችና የሃይማኖቶ አባቶች በተገኘበት እየተከበረ ይገኛል።

በሐረር ከተማ በሚገኘው ኢማም አህመድ ስታድየም በዓሉ  በቨብዙ ሺ የሚቆጠሩ የሙስሊሙ ማህበረሰብ በተገኙበት እየተከበረ ይገኛል።