የሲዳማ የዘመን መለወጫ በዓል በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው

105

ሀዋሳ ፤ ሚያዚያ20/ 2014 (ኢዜአ) የሲዳማ የዘመን መለወጫ የፊቼ ጨምባላላ በዓል በሲምፖዚየምና ሌሎች ዝግጅቶች በሀዋሳ ከተማ እየተከበረ ነው።

በሲዳማ ባህል አዳራሽ  እየተካሄደ  ባለው ሲምፖዚየም ላይ  የፊቼ ጫምባላላ ባህላዊ እሴቶች ዙሪያ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ጥናታዊ ጽሁፎች እንደሚቀርቡ ይጠበቃል።

በዛሬው የበዓሉ ዋዜማ  የ"ሻፌታ" ሥነ-ሥርዓትን ጨምሮ ሌሎችም  ዝግጅቶች  እንደሚኖሩ ተመልክቷል።

በሥነ-ሥርዓት ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ ፣ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳና የደቡብ ክልል ምክር ቤት አፈ- ጉባኤ ወይዘሮ ፋጤ ሰርሞሎና የዞን አመራሮች ተገኝተዋል።

የመጀመሪያው የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አባተ ኪሾ፣ አምባሳደር ሽፈራው ሽጉጤና  አምባሳደር ደሴ ዳልኬ ጨምሮ ሌሎችም እንግዶች መታደማቸውን ኢዜአ  ከሥፍራው ዘግቧል

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም