በገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ የተመራ ልዑክ ከአሜሪካ የተለያዩ ተቋማት የስራ ሃላፊዎች ጋር ተወያየ

146

ሚያዝያ 17 ቀን 2014 (ኢዜአ) በገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሺዴ የተመራ ልዑክ ከአሜሪካ የተለያዩ ተቋማት የስራ ሃላፊዎች ጋር ተወያየ።

ልዑኩ ከአሜሪካ የግምጃ ቤት፣ የውጭ ጉዳይ፣ የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት፣ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ እና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ጋር ውጤታማ ውይይት አድርጓል።

በውይይቱ ወቅት በኢትዮጵያና አሜሪካ ታሪካዊ፣ ስትራቴጂክ እና በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ መምከራቸው ተጠቅሷል፡፡

ውይይቱ በዋናነት በኢትዮጵያ ብሎም በአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ልማቶች ላይ ትኩረቱን ያደረገ እንደነበረ የገንዘብ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።