የትንሳኤ በዓል መጪው ጊዜ የተሻለ ይሆናል ብለን ተስፋ የምናደርግበት መልካምነት አሸናፊ ይሆናል ብለን የምናምንበት ነው- አምባሳደር ኢቭጌኒ ተረክሂን

ሚያዝያ 16 ቀን 2014 (ኢዜአ)“የትንሳኤ በዓል መጪው ጊዜ የተሻለ ይሆናል ብለን ተስፋ የምናደርግበት መልካምነት አሸናፊ ይሆናል ብለን የምናምንበት ነው” ሲሉ በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኢቭጌኒ ተረክሂን ገለጹ።

የበዓሉ ደስታ አዳዲስ መልካም ነገሮችን የማድረግ ጅማሬ ነው ብለዋል።

በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኢቭጌኒ ተረክሂን “ለሁሉም የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ለትንሳኤው በዓል እንኳን አደረሳችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እወዳለሁ” ብለዋል።

የትንሳኤ በዓል ደስታ አዳዲስ መልካም ነገሮችን የማድረግ ጅማሬ እንዲሁም የተቸገሩትና መርዳትና በአንድነት ውስጥ ሰላምና መስማማትን መፍጠሪያ መሆኑን ገልጸዋል።

በዓሉ መጪው ጊዜ የተሻለ ይሆናል ብለን ተስፋ የምንሰንቅበትና መልካምነት ያሸንፋል ብለን እንድናምን የሚያደርገን ነው ብለዋል።

በጋራ ስንሆንና ተመሳሳይ እሴቶች ስንጋራ ሁሉም ፈተናዎች ማለፍ እንዲሁም ደስታና ብልጽግና ላይ መድረስ እንደሚቻል አመልክተዋል።

አምባሳደር ኢቭጌኒ ተረክሂን ለሁሉም የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች የትንሳኤ በዓል የሰላም፣የጤናና የደስታ እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን እንዳስተላለፉ በአዲስ አበባ የሚገኘው የሩሲያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም