ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የትንሳኤን በዓል ምክንያት በማድረግ ለጎዳና ተዳዳሪና አቅመ ደካሞች ማዕድ አጋሩ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የትንሳኤን በዓል ምክንያት በማድረግ ለጎዳና ተዳዳሪና አቅመ ደካሞች ማዕድ አጋሩ

ሚያዝያ 16 ቀን 2014 (ኢዜአ)ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የትንሳኤን በዓል ምክንያት በማድረግ ለጎዳና ተዳዳሪና አቅመ ደካሞች በቤተ መንግሥት ማዕድ አጋሩ፡፡
የትንሳኤን በዓል ምክንያት በማድረግ የምሳ ግብዣ የተደረገላቸው 230 ጧሪ የሌላቸው አረጋውያን፣ የጎዳና ተዳዳሪዎች፣ቤተሰብ የሌላቸው ህፃናትና ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው አቅመ ደካሞች ናቸው፡፡
በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት ተሳታፊዎች ለኢዜአ እንዳሉት፤ ቀና ብለን አይተነው በማናውቀው ቤተ መንግስት የምሳ ግብዣ ስለተደረገልን እናመሰግናለን፡፡