በአቶ ተስፋዬ ኡርጌ ጉዳይ ተጨማሪ ምርመራ ለማካሄድ ፖሊስ የጠየቀው የ10 ቀን ጊዜ ቀጠሮ ተፈቀደ

72
አዲስ አበባ ጳጉሜን 1/2010 የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት 10ኛ ወንጀል ችሎት በአቶ ተስፋዬ ኡርጌ ጉዳይ ተጨማሪ ምርመራ ለማካሄድ ፖሊስ የጠየቀውን የ10 ቀን ጊዜ ቀጠሮ  ተፈቀደ። ከሰኔ 16 የቦንብ ጥቃት ጋር በተያያዘ የቦንቡን ጥቃት በማቀነባበር በተጠረጠሩት አቶ ተስፋዬ ኡርጌ ተጨማሪ ምርመራ ለማካሄድ ፖሊስ ከጠየቀው የ10 ቀን ጊዜ ቀጠሮ ፈቀደ። በቁጥጥር ሥር የሚገኙትና በቀድሞ የጸር ሽብር ግብር ኃይል ኃለፊ በነበሩት አቶ ተስፋዬ ዛሬ ችሎት ቢቀርቡም የሰው፣ የሰነድ እንዲሁም የቀረጻ የድምጽ ማስረጃ ለማሰባሰብ በሚል ፖሊስ የጠየቀው ተጨማሪ ጊዜ 14 ቀን ቢሆንም ፍርድ ቤቱ የፈቀደው ግን 10 ቀን ነው። የስልክ ልውውጥን የተመለከተ መረጃ፤ ከብሔራዊ መረጃ ደህንነት ሰራተኞች ጋር ተያያዥ ያለው የድምጽ ቅጅ እና በመስራያ ቤቱ ከሚሰሩ ሰራተኞች ጋር ግንኙነት ያለና ውሰብስብ በመሆኑ የምርመራ ስራዎችን ለማከናወንም ተጨማሪ ጊዜ እንደሚያስፈልግ በመግለጽ ፖሊስ ለችሎቱ ተጨማሪ ጊዜ ቀጠሮ ጠይቋል። ተጠርጣሪው በበኩላቸው "የተጠየቀው ጊዜ በዝቷል፤ በተደጋጋሚ ለፍርድ ቤት የዋስትና መብት ባቅርብም ምንም ውሳኔ አልተሰጠኝም፤ ልንለቀቅ ይገባል'' የሚል ጥያቄ አንስተዋል፡፡ በተጨማሪም "ፖሊስ ተጨማሪ ምርምራ ያስፈለገኛል በሚል ሰበብ የዋስትና መብቴ ተከልክሎ እየተጉላላሁ በመሆኑ ፍርድ ችሎቱ እንዲያይልኝ" ሲሉም ጠይቀዋል። ግራ ቀኙን የመረመረው ችሎቱም የተጠርጣሪውን የዋስትና ጥያቄ ውድቅ በማድረግ ለፖሊስ የ10 ቀናት ቀነ ቀጠሮ በመፍቀድ ለመሰከረም 5 ቀን 2011 ዓ.ም ቀጥሯል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም