ኢየሱስ ክርስቶስ በጸሎተ ሐሙስ ያስተማረውን ትህትና ህዝበ ክርስቲያኑ በእለት ተለት ኑሮው ሊተገብረው ይገባል

156

ሚያዚያ 13 ቀን 2014 (ኢዜአ) ኢየሱስ ክርስቶስ በጸሎተ ሐሙስ ያስተማረውን ፍቅርና ትህትና ህዝበ ክርስቲያኑ በእለት ተለት ኑሮው ሊተገብረው ይገባል ሲሉ ኢዜአ ያነጋገራቸው የእምነቱ ተከታዮች ገለጹ።

የጸሎተ ሐሙስ በዛሬው እለት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አብያተ ክርስቲያናት እና ገዳማት በተለያዩ መንፈሳዊ ሥነ-ሥርዓቶች ተከናውኗል።

በመንበረ ፓትሪያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ከማለዳው አንስቶ የተለያዩ መንፈሳዊ ሥነ-ሥርዓቶች የተከናወኑ ሲሆን በመርሐ-ግብሩም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስን ጨምሮ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ ካህናት እና በርካታ ምዕመናን ተገኝተዋል።

የዐቢይ ጾም 8ተኛ ሳምንት ኢየሱስ ክርስቶስ የድህነት እና የቅዱስ ቁርባን ስርዓትን የመሰረተባትና ዝቅ ብሎ የሐዋርያቱን እግር በማጠብ ትህትናን ያስተማረበት መሆኑን የሓይማኖት አባቶች ይገልጻሉ።

በዚህም ክርስቶስ ያስተማረውን ፍቅር እና ትህትና ህዝበ ክርስቲያኑ ሊተገብረውው እንደሚገባም ነው ኢዜአ ያነጋገራቸው የእምነቱ ተከታዮች የሚገልጹት።  

በዚህም ዝቅ ብሎ ሰዎችን ማክበር፣ መታዘዝና ማገልገል እንደሚገባም ተናግረዋል።   

እለቱ የተለያዩ ስያሜዎች ያሉት ሲሆን ክርስቶስ ያደረገውን ጸሎት ተከትሎ ጸሎተ ሐሙስ፣ የሀዲስ ኪዳኑ ሐሙስ፣ የምሥጢር ቀን እና ሕጽበተ-እግር የሚል ስያሜም እንዳለው የሃይማኖት አባቶች ያስረዳሉ።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም