ደቡብ ሱዳን የውጭ እርዳታ ሰራተኞችን አስገድደው ደፍረዋል በሚል 10 ወታደሮችን በእስራት ቀጣች

105
ጳጉሜ 1/2010 የሀገሪቱ ወታደራዊ ፍርድ ቤት በዋለው ችሎት የውጭ እርዳታ ሰራተኞችን አስገድደው የደፈሩና አንድ ጋዜጠኛን የገደሉ ወታደሮችን ከ7 እስከ እድሜ ልክ እስራት ፈርዶባቸዋል። ፍርድ ቤቱ የደቡብ ሱዳን መንግስት በአስገድዶ መድፈር ለተጎዱ የእርዳታ ሰራተኞች ለእያንዳንዳቸው 4 ሺህ የአመሪካን ዶላር ካሳ እንዲከፍል ወስኗል። እንድ ተከሳሽ ወታደር ከድርጊቱ ነጻ ነው በሚል የተለቀቀ ሲሆን ሌላ ተከሳሽ ደግሞ በእስር ላይ እያለ በተፈጥሯዊ ምክንያት ሞቷል። ወንጀሉ በፈረንጆቹ 2016 በሀገሪቱ ዋና ከተማ ጁባ ቴራይን ሆቴል የተፈጸመ ነው፡፡ በወቅቱ የደቡብ ሱዳን መንግስትና አማጽያን ሃይሎች ጁባ ውስጥ ከባድ ወጊያ ሲያደርጉ ነው ጠቃቱ የደረሰው። በዚያ ውጊያ ሁለት የተባበሩት መንግስታት ሰላም አስከባሪዎችን ጨምሮ ከ70 በላይ ሰዎች ማለፋቸው ይታወሳል። በሆቴሉ ተጠልለው የነበሩ 5 ሴት የውጭ እርዳታ ሰራተኞችም በወታደሮች አስገድዶ መድፈር እንደተፈፀመባቸው ተመላክቷል። የደቡብ ሱዳን ወታደራዊ ፍርድ ቤት ሆቴላቸው ለወደመባቸው ባለንብረቶች ከ2 ሚሊየን ዶላር በላይ ካሳ እንዲከፍልም ትዕዛዝ ሰጥቷል። ምንጭ፦ቢቢሲና ሮይተርስ  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም