በአፍሪካ ድርቅን ለመቅረፍ የግብርናውን ዘርፍ የምግብ አቅርቦት ማሳደግ ያስፈልጋል

652

ሚይዝይ 3/2014 /ኢዜአ/ በአፍሪካ የሚታየውን የድርቅ ችግር ለመቅረፍ የግብርናውን ዘርፍ የምግብ አቅርቦት መለወጥ እንደሚያስፈልግ በፋኦ የአፍሪካ ተጠባባቂ ዋና ዳይሬክተር አበበ ኃይለገብርኤል አመለከቱ።

የአለም የምግብና እርሻ ድርጅት(ፋኦ) የአፍሪካ ቅርንጫፍ 32ኛው አህጉር አቀፍ የምክክር መድረክ በኢኳቶርያል ጊኒ ማላቡ እየተካሄደ ነው።

በዚህ ወቅት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የድርጅቱ ተጠባባቂ ዋና ዳይሬክተር አበበ ኃይለገብርኤል በአፍሪካ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የግብርናውን ዘርፍ አካታች ማድረግ ናችግሮችን መቋቋም የሚያስችል የረጅም አመት እቅዶችን መንደፍ ያስፈልግጋል ብለዋል።

በተለይም በአህጉሩ የሚከሰተውን የድርቅ ችግር ለመቅረፍ የግብርናውን ዘርፍ የምግብ አቅርቦት አሰራር መለወጥ ያስፈልጋል ነው ያሉት።

በመድረኩ ላይ በአፍሪካ ሕብረት የዘርፉ ከፍተኛ ባለሙያዎች እየተሳፉ ሲሆን የግብርናውን የምግብ አቅርቦት ችግር የሚያመለክቱና መፍትሔ ሰጪ የሆኑ ጉዳዮች ይዳሰሱበታል ተብሎ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም