ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች የተካፈሉበት የአፍጥር ስነ-ስርዓት በጅማ ተካሄደ

96

ጅማ፣መጋቢት 26 ቀን 2014 (ኢዜአ) ሚኒስትሮችና ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች የተካፈሉበት የረመዳን የአፍጥር ስነ-ስርዓት በጅማ ከተማ ተካሄዷል።

የአፍጥር ስነ-ስርዓቱ "ለሀገራችን አንድነትና ፍቅር" በሚል መሪ ሀሳብ ነው የተካሄደው።

የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ፣ የቱሪዝም ሚኒስትር ወይዘሮ ናሲሴ ጫሊ፣የመንገዶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ሀብታሙ ተገኝ በአፍጥር ስነ-ስርዓቱ ላይ ተካፍለዋል።

ሚኒስትሮቹና የስራ ሀላፊዎቹ ዛሬ በጅማ ከተማ ጀሬን መናገሻ ላይ የሚገኘውን የንጉሥ አባጅፋርን ቤተ መንግስት የእድሳት ሂደትን የደረሰበትን ሁኔታ ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም