የሲዳማ ክልልን ከቡና ልማት በተጓዳኝ የእንስሳት ሀብት ማዕከል ማድረግ ይገባል - ኢዜአ አማርኛ
የሲዳማ ክልልን ከቡና ልማት በተጓዳኝ የእንስሳት ሀብት ማዕከል ማድረግ ይገባል

መጋቢት 25 2014(ኢዜአ) የሲዳማ ክልልን ከቡና ልማት በተጓዳኝ የእንስሳት ሀብት ልማት ማዕከል ማድረግ እንደሚገባ ተመላከተ።
የኢትዮጵያ ኀብረት ስራ ኮሚሽን ልዑክ በሲዳማ ክልል ሀዋሳ ከተማ የኤልቶ የገበሬዎች ሁለገብ ኀብረት ስራ ማኀበርን የስራ እንቅሰቃሴ ጎብኝቷል።
በዚህ ወቅት የኢትዮጵያ ኀብረት ስራ ኮሚሽነር ወይዘሮ ፍሬዓለም ሺባባዉ "ከቡና በተጓዳኝ የሲዳማ ክልልን በእንስሳት ሀብት ለአብነት ያህል የዶሮ ማዕከል (ቺክን ሀብ) ማድረግ እንችላለን” ብለዋል።
በክልሉ ከዩኒቨርሲቲ የወጡ የእንስሳት ሳይንስ ባለሙያዎችን አደራጅተን በሳይንሳዊ መንገድ ወደ ዶሮ ማርባት ስራ እንዲገቡም መስራት አለብን ነው ያሉት።

የኤልቶ ዩኒየን ደረጃውን የጠበቀ የእንስሳት መኖ ማቀናበሪያ ፋብሪካ መኖሩ መልካም ዕድል ነው ያሉት ኮሚሽነሯ በውስን ምርቶች ላይ (ቡና) ላይ ብቻ ተማምነን ምርቱ ላይ በተገማች እና በማይገመቱ ምክንያቶች ችግር ተፈጥሮ ገበሬዎቻችን ላይም ህዝባችን ላይ ችግር መፈጠር የለበትም ብለዋል።
ከኮሚሽኑ እንዳገኘነው መረጃ የልዑክ ቡድኑ የዩኒየኑን የሰብል ማከማቻ መጋዘን፣ የእንስሳት መኖ ማቀናበሪያ እና በ113 ሚሊዩን ብር ወጪ እየተገነባ ያለውን የከረጢት ፋብሪካም ጎብኝቷል።