የኦሮሚያ የባህል ሳምንት በሻሸመኔ ከተማ እየተካሄደ ነው

82

መጋቢት 18 ቀን 2014 (ኢዜአ) “ባህላችን ለቱሪዝም ዕድገታችን” በሚል መሪ ሀሳብ በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የባህል ሳምንት (ፌስቲቫል) በምዕራብ አርሲ ዞን ሻሸመኔ ከተማ ከመጋቢት ከዛሬ 18 እስከ 20 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ይካሄዳል፡፡

በዚህም በጠዋቱ በጎዳና ላይ ትርዒት መከበር ጀምሯል፡፡

ከክልሉ በተጨማሪ የሌሎች ክልሎች የባህል ቡድን አባላት በተጋባዥነት በባህል ሳምንቱ እየተሳተፉ ነው፡፡

በባህል ሳምንቱ ላይ ሁሉም የኦሮሚያ ክልል ዞኖች የባህል ቡድኖች የሚሳተፉ ሲሆን በጎዳና ላይ ትርዒት፣ የባህል ኢንዱስትሪ ምርቶች አውደርዕይ፣ በተለያዩ ሙዚቃ ባንዶች መካከል ውድድር ይቀርብበታል ተብሎ ይበቃል፡፡

የፓናል ውይይት እንዲሁም የጥናትና ምርምር ሲፖዚየምም የባህል ሳምንቱ አካል እንደሚሆን ተነግሯል።

ለኦሮሞ ባህልና ኪነጥበብ ዕድገት አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላት እውቅናና ምስጋና የሚሰጥ ይሆናልም፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም