የውጭ ኦዲት ድግግሞሽን የሚያስቀር ረቂቅ መመሪያ ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው

116

መጋቢት 17 ቀን 2014 (ኢዜአ) የፌደራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት የውጭ ኦዲት ድግግሞሽን ለማስቀረት የሚያስችል የነጠላ ኦዲት መምሪያ ላይ ውይይት እያካሄደ ነው።

በዚህ ወቅት የፌደራል ዋና ኦዲተር የኦዲት ዘርፍ ምክትል ዋና ኦዲተር ወይዘሮ መሠረት ደምሴ እንዳሉት በፌደራልና በክልል ደረጃ ተመሳሳይ ኦዲት ላለማድረግና ድግግሞሽን ለማስቀረት የሚያስችል መመሪያ ተዘጋጅቷል።

መመሪያው በሕገመንግሥቱ አንቀጽ 94(2) መነሻነት የፌዴራልና የክልል ዋና ዋና ኦዲተሮች በጋራ እንዳዘጋጁት ገልጸው የዚህ መመሪያ አላማ በነጠላ ኦዲት አፈጻጸም ላይ ግልጽ የሆነ የአሰራር ስርዓት ለመገንባት ነው ብለዋል።

መመሪያው እንደ ኢትዮጵያ ተመሣሣይ የኦዲት አተገባበር ካላቸው ሀገራት ልምድ ተወስዶ መዘጋጀቱንም አመልክተዋል።

ይህ መመሪያ የፌዴራልና የክልል ኦዲተር መስሪያ ቤቶች አንድ አይነት ኦዲት እንዳያደርጉ፣ የአፈጻጸም አቅምን ለማሳደግና የሀብት ብክነትን ለማስቀረት ያስችላል ብለዋል።

የዛሬው መድረክም መመሪያው ወደ አተገባበር ከመግባቱ በፊት ከክልል የኦዲተር መሥሪያ ቤቶች ጋር ለመወያያት ያለመ መሆኑን ገልጸዋል።

አዋጁ በያዛቸው ሀሳቦች ላይ የክልልና የፌዴራል ኦዲተር ተወካዮች አስተያየት እየሰጡበት ይገኛል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ

‼️

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ

‼️

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ

‼️

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ

‼️
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም