ህዝባዊ የውይይት መድረክ ዛሬ በሠመራ ከተማ ተጀመረ

ሠመራ፤ መጋቢት 15/2014(ኢዜአ) "የፈተናዎች መብዛት ከብልጽግና ጉዟችን አያስቆመንም" በሚል መሪ ሀሳብ በአፋር ክልል ሠመራ ከተማ የተዘጋጀ ህዝባዊ የውይይት መድረክ ዛሬ ተጀመረ።

የውይይት መድረኩን እየመሩ ያሉት የብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት አቶ አወል አርባ፣  አቶ አህመድ ሺዴ እና አቶ ተስፋዬ ይገዙ ናቸው።

ከ1ሺ በላይ የሠመራ-ሎጎያ ከተማ ነዋሪ የሆኑ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እየተሳተፉ ነው።

በተመሳሳይ የውይይት መድረኮች በክልሉ ሁሉም ወረዳዎችና ዞን ማዕከላት እየተካሄደ መሆኑን የብልጽግና ፓርቲ የአፋር ክልል ጽህፈት ቤት መግለጹን ጠቅሶ ኢዜአ ከሠመራ ዘግቧል።

በሀገሪቱ የተለያዩ ከተሞች ተመሳሳይ የውይይት መድረኮች ትናንት ሲካሄዱ መዋላቸውን በወቅቱ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም