ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በምስራቅ ሸዋ ዞን አዳማ ወረዳ ወንጂ ኩሪፍቱ በመስኖ የለማ ስንዴን ጎበኙ

284

መጋቢት 13 ቀን 2014 (ኢዜአ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በምስራቅ ሸዋ ዞን አዳማ ወረዳ ወንጂ ኩሪፍቱ በ564 ሄክታር መሬት ላይ በመስኖ የለማ ስንዴን ጎበኙ።

በጉብኝቱ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ በተጨማሪ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ሽመልስ አብዲሳ፣ በዓለም ባንክ የአፍሪካ ዳይሬክተር ዑስማን ዲዮን፣ የዓለም ባንክ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ታውፊላ ኒያምድዛቦ፣ እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

ልኡካኑ በምስራቅ ሸዋ ዞን አዳማ ወረዳ ወንጂ ኩሪፍቱ ቀበሌ በ564 ሄክታር መሬት በመስኖ የለማ የስንዴ አዝመራ ጎብኝተዋል።በኦሮሚያ ክልል በመጀመሪያ ዙር የመስኖ ልማት የለማው የስንዴ አዝእርት እየተሰበሰበ ሲሆን የሁለተኛ ዙር የመስኖ ልማት ስራ ለማስጀመር የመሬት ዝግጅት እየተከናወነ ይገኛል።