በምግብ ራሳችንን ለመቻል ምርታማነታችንን ማፋጠን በእጅጉ ያስፈልገናል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

78

መጋቢት 11 ቀን 2014 (ኢዜአ)ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የስንዴ አቅርቦት በዓለም አቀፍ ሁነቶች ጫና እየደረሰበት በመሆኑ፣በምግብ ራሳችንን ለመቻል ምርታማነታችንን ማፋጠን በእጅጉ ያስፈልገናል'' ሲሉ ተናገሩ።

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሚመራ የሚኒስትሮችና የክልል ርእሰ መስተዳደሮች ልዑካን ቡድን በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ምዕራብ ደንቢያ ወረዳ ዋዋ ቀበሌ የበጋ መስኖ ስንዴ ልማትና የጎርጎራ ገበታ ለሃገር ፕሮጀክትን እየጎበኘ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዛሬው እለት ጉብኝታቸው በአማራ ክልል ማዕከላዊ ጎንደር ዞን ምዕራብ ደንቢያ ወረዳ ዋዋ ቀበሌ በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የታየው ምርታማነት ተስፋ ሰጪ ነው ብለዋል።

''የግብርና ጉዟችን አድካሚ ሊሆን ይችላል፣ ነገር ግን ተጋድሏችን የምርታማነታችንን መጠን በሚልዮኖች ለማስፋፋት ነው''በማለት በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም