በይርጋጨፌ ወረዳ በደረሰ የተሽከርካሪ አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት አለፈ

133

ዲላ መጋቢት 9/2014 (ኢዜአ) በጌዴኦ ዞን ይርጋጨፌ ወረዳ በደረሰ የተሽከርካሪ አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ ።

የይርጋጨፌ ወረዳ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት የትራፊክ ክፍል ቁጥጥርና ክትትል ግንዛቤ መፍጠሪያ ቡድን መሪ ረዳት ኢንስፔክተር ቸርነት ጀቦ ለኢዜአ እንደገለጹት አደጋው  የደረሰው ዛሬ ማለዳ በወረዳው ወቴ ቀበሌ ነው።

የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3 -31041 አአ የሆነ የጭነት ተሽከርካሪ  ቡና ጭኖ ከኮቾሬ ወረዳ ጨለለቅቱ ከተማ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ እያለ በግምት 150 ሜትር ጥልቀት ባለው ገደል ውስጥ በመግባቱ አደጋው መድረሱን ተናግረዋል።

በአደጋው አሽከርካሪውና ረዳቱ ሕይወታቸው ውድያው  ማለፉን አመልክተዋል ።

ተሽከርካሪውና ለማዕከላዊ ገበያ የተጫነው ቡና ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ውጭ መሆኑን ገልጸዋል ።

የአደጋው መንስኤ እየተጣራ መሆኑን አመልክተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም