ብልጽግና ለህዝብ ሰላም፣ ፍትህና ዴሞክራሲ እውን መሆን እየተጋ ያለ ህብረ ብሔራዊ ፓርቲ ነው

59

መጋቢት 2/2014/ኢዜአ/ ብልጽግና ለህዝብ ሰላም፣ ፍትህና ዴሞክራሲ እውን መሆን እየተጋ ያለ ህብረ ብሔራዊ ፓርቲ መሆኑን የፓርቲው ዋና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አደም ፋራህ ተናገሩ።

የብልጽግና ፓርቲ አንደኛ ጉባኤ የሥራ አስፈጻሚና ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት እንዲሁም የውጭና የአገር ውስጥ ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት መካሄድ ጀምሯል።

በጉባኤው መክፈቻ ላይ የፓርቲው ዋና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አደም ፋራህ፤ ባስተላለፉት መልእክት ብልጽግና ለህዝብ ሰላም፣ ፍትህና ዴሞክራሲ እውን መሆን እየተጋ ያለ ህብረ ብሔራዊ ፓርቲ መሆኑን ገልጸዋል።

የሕዝቡን የሰላምና የልማት ጥያቄ በዘላቂነት ለመፍታት እየሰራ ያለ ህዝባዊ ፓርቲ ስለመሆኑም ጠቅሰዋል።

ፓርቲው የሕዝቦችን ወንድማማችነት ማዕከል አድርጎ ሕብረ ብሔራዊ አንድነትን ለማጠናከር በትጋት እየሰራ መሆኑንም ኃላፊው ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ እውነተኛ የዴሞክራሲያዊ ስርዓት በመገንባት የሕዝቡን ፍላጎትና ጥቅም ለማስከበር እየሰራ ይገኛል ብለዋል።

በየጊዜው የሚያጋጥሙትን ጉድለቶች እየሞላ የለውጥና ቀጣይነት ያለው ልማት እየሰራ ያለ ፓርቲ መሆኑንም ነው አቶ አደም የተናገሩት።

ብልጽግና አመራሮችንና አባላትን የማጥራት እንቅስቃሴ ላይ መሆኑን ጠቅሰው፤ በቅርብ ጊዜ እየተከናወነ ባለው የውስጥ ፓርቲ የማጠናከሪያ ሥራዎች እርምጃ እየተወሰደ ተጨባጭ ለውጥ መምጣቱንም ገልጸዋል።

የአሁኑ ጉባኤም ይህንኑ የሚያጠናክሩ ውሳኔዎች የሚተላለፉበት ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም