የብልጽግና ፓርቲ 1ኛ ጉባኤ የመክፈቻ ሥነ ስርዓት እየተካሄደ ነው

መጋቢት 02 ቀን 2014 (ኢዜአ) የብልጽግና ፓርቲ 1ኛ ጠቅላላ ጉባኤ “ከፈተና ወደ ልዕልና!” በሚል መሪ ሀሳብ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል፡፡

በአሁኑ ወቅት የጉባኤው የመክፈቻ ስነ-ስርዓት የብልፅግና ፓርቲ ፕሬዚዳንትና የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ የጉባኤው ተሳታፊዎች፣ የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተወካዮች፣ የውጭ ሀገራት ወዳጅ ፓርቲዎች ተወካዮች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት እየተካሄደ ይገኛል።

ከዛሬ ጀምሮ ለሶስት ቀናት የሚቆየው የፓርቲው የመጀመሪያ ጉባኤ የኢትዮጵያውያንን ሁለንተናዊ ብልጽግና የሚያረጋግጡ ውሳኔዎች እንደሚተላለፉበት ፓርቲው አስታውቋል።

በጉባኤው 1 ሺህ 600 የፓርቲው አባላት በድምፅ የተሳተፉ ሲሆን፥ 400 ከተለያየ የህብረተሰብ ክፍሎች እና ከውጭ ሀገራት የተጋበዙ እንግዶች ያለ ድምፅ በመሳተፍ ላይ ናቸው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም