በጦርነትና ድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ገቢ ማሰባሰቢያ 9400 አጭር የፅሑፍ መልዕክት መላኪያ ይፋ ሆነ

141

የካቲት 29 ቀን 2014 (ኢዜአ) ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በጦርነትና ድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ገቢ ማሰባሰቢያ የሚሆን 9400 አጭር የፅሑፍ መልዕክት መላኪያ ይፋ አደረጉ።

የአጭር የፅሑፍ መልዕክት የድጋፍ ማሰባሰቢያ መርኃ ግብሩ ለአንድ ዓመት የሚቆይ ነው።

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የበላይ ጠባቂና የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ “እኔም ለወገኔ” በሚል መሪ ቃል በድርቅና በጦርነት ለተጎዱ ወገኖች የድጋፍ ማሰባሰቢያ መርኃ ግብርን ዛሬ በይፋ አስጀምረዋል።

በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ በድርቅና ጦርነት ምክንያት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ወገኖች በተለይም ሴቶች፣ ህጻናት እና አረጋውያን ለከፋ ሰብዓዊ ችግር መጋለጣቸው ተነግሯል።

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የተጎጂ ወገኖችን ህይወት ለመታደግ ሰብዓዊ ድጋፉን “እኔም ለወገኔ” በሚል መሪ ቃል አጠናክሮ ለመቀጠል አስቸኳይ የልገሳ ማሰባሰቢያ መርሀ ግብር በመተግበር ላይ መሆኑንም ገልጿል።

በዛሬው ዕለትም የማህበሩ የበላይ ጠባቂ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በአጭር የፅሑፍ መልዕክት ድጋፍ ማሰባሰብ የሚያስችለውን 9400 ይፋ አድርገዋል።

በዚህም ድጋፍ ማድረግ የሚፈልጉ ወገኖች ወደ 9400 "OK" ብለው በመላክ ከአንድ ብር ጀምሮ መለገስ እንደሚችሉም ተነግሯል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

‼

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ

‼

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ

‼

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ

‼
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም