የምግብ ዘይት እጥረትን በጊዜያዊነት ለመፍታት 40 ሚሊየን ሊትር ወደ አገር ውስጥ ሊገባ ነው

312

የካቲት 28 ቀን 2014 (ኢዜአ) በአገሪቱ ሰሞኑን ያጋጠመውን የምግብ ዘይት እጥረትን በጊዜያዊነት ለመፍታት 40 ሚሊዮን ሊትር የምግብ ዘይት በቅርቡ ወደ አገር እንደሚገባ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ገለጸ።

ሰሞኑን በምግብ ዘይት ላይ የታየውን የዋጋ ጭማሪ አስመልክቶ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር፣ የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ እንዲሁም የኦሮሚያ ንግድ ቢሮ ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

በንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የንግድ እቃዎች ዋጋ ቁጥጥር ጥናትና ክትትል ዳይሬክተር ወይዘሮ መስከረም ባህሩ፤ ሰሞኑን በዘይት ላይ የዋጋ ጭማሪ የታየበት ዋና ምክንያት በዓለም አቀፍ ደረጃ በዘይት ምርት ላይ የዋጋ ጭማሪ በመከሰቱ ነው ብለዋል።

በዚህም ምክንያት እንደ አገር የዘይት ምርት እጥረት ማጋጠሙን ገልጸው፤ ችግሩን በጊዜያዊነት ለመፍታት 40 ሚሊየን ሊትር የምግብ ዘይት በልዩ ሁኔታ በቅርቡ ወደ አገር እንደሚገባ ተናግረዋል።