ጤና ሚኒስትሯ በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የንግስት ኢሌኒ መሀመድ መታሰቢያ ሆስፒታል የሲቲ ስካን ማሽን ስራ አስጀመሩ

102

ሆሳዕና የካቲት 27/2014 (ኢዜአ) የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በዋቸሞ ዩንቨርስቲ የንግስት ኢሌኒ መሀመድ መታሰቢያ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል  ከ45 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ ተደርጎበት የተተከለ የሲቲ ስካን ማሽን መርቀው ስራ አስጀመሩ ።

ሚኒስትሯ በሆስፒታሉ ከ2 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር  በላይ ወጭ ለሚገነባው  የኦክስጅን ማምረቻና የእናቶችና  ህፃናት ጤና አገልግሎት መስጫ ማእከል የመሰረተ ድንጋይ አስቀምጠዋል ።

የንግስት ኢሌኒ መሀመድ መታሰቢያ  ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በ1973 ዓ.ም ግንባታው ተጠናቆ  የህክምና አገልግሎት  መስጠት መጀመሩ ይታወሳል ።

በስነ ስርአቱ ላይ የደቡብ ክልል ጤና  ቢሮ ኃላፊ አቶ እንዳሻው ሽብሩን ጨምሮ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎችና   ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም